ሠልጣኝ አመራሮች የተለያዩ የልማትእና የኢንቨስትመንት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛል።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ የሁለተኛው ዙር የአቅም ግንባታ ሰልጣኝ የአመራሮች በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማትና ኢንቨስትመንት ስራዎችን ተዘዋውሮ እየጎበኙ ይገኛል።

“የህልም ጉልበት፤ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል ባለፉት አንድ ሣምንት በቦንጋ ከተማ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመከታተል ላይ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ የአመራሮች በከተማው በእንስሳት እርባታና ወተት ምርት የተሰማራውን የአባይነሽ ፋርም እየጎበኙ ይገኛል።

“የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚሰጠው በዚህ የሁለተኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና በክልሉ 683 አመራሮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ የገለጹት የክልሉ ረዳት የመንግሥት አቶ ነጋ አበራ ጉብኝቱ ሰልጠኞቹ በንድፈ ሀሳብ ያገኙት እውቀት ከነባራዊ እውነታዎች ጋር በንጽጽር እንዲመለከቱ የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል።

በየደረጃው ያለው አመራር በፓርቲው መሪነት የተገኙ እምርታዊ ለውጦችን በመቀመር ወደ መጡበት ስመለሱ የልማት አቅሞችን አሟጦ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት አድርጎ መሠራት እንዳለበት ያስገነዘቡት አቶ ነጋ ጉብኝቱ የብልጽግና ፓርቲ ‘ኢንሼቲቭ’ ውጤታማ መሆናቸውን በተግባር ያመላከተ መሆኑን ገልጸዋል።

ለጎቢኚዎቹ ገለጻ የሰጡት የአባይነሽ ፋርም ስራ አስኪያጅ አቶ መሠረት አቤ ፋርሙ በ24 የወተት ላሞች እንዳሉትና በቀን በአማካይ ከ500 ሊትር በላይ የወተት ምርት ለአከባቢ ገበያ እየቀረበ መሆኑን አስረድተዋል።

በፈረንጆቹ 2016 በቤተሰብ ደረጃ አራት ላሞችን በመያዝ የተጀመረው የእርባታ ስራ አሁን ላይ ከ80 በላይ የውጭ ዝርያ ያላቸው ለሞች እንዳለው ነው ያስረዱት።

ድርጅቱ ከወተት ምርት ባሻገር በድቀላ አገልግሎት እንዲሁም የተቀነባበረ መኖ በማዘጋጀት እስከ ሚዛን፣ ቴፒ፣ ጅማ፣ ቦንጋና ሌሎች የካፋ ዞን ወረዳዎች ድረስ ደንበኛ በማፍራት ምርቱን እያደረሰ እንደሚገኝ የገለጹት ስራ አስኪያጁ በቀጣይ የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው ጊደር በማቅረብ እንዲሁም የኮርማ ጣቢያ በማቋቋም የአከባቢው አርሶ አደሮች በተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ፋርሙ የአከባቢ ማህበረሰብን በተለያየ መልኩ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ያብራሩት አቶ መሠረት በተላይ በዝርፊያ ማሻሻያ፣ መኖ አቅርቦት እንዲሁም በሰው ሰራሽ የማዳቀል አግልግሎት እየሰጠ እንደሆነም ጨምረው ገልጸዋል።

የወተት ልማት ድርጅቱ በአጠቃላይ ከ60 ባላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን የገለጹት አቶ መሠረት ድርጅቱ ቀጣይ በወተት ልማት ፣ በከብት ድለባና የዝርፊያ ማሻሻያ ስራዎችን ለማስፋፋት እቅድ ይዞ ወደ ተግባር መግባቱን በመጥቀስ መንግሥት እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በጉብኝቱ የተሳተፉ ሰልጣኝ የመንግሥት አመራሮች በበኩላቸው ጉብኝቱ ቁጭትና ተስፋ እንደፈጠረባቸው በመግለጽ ቀጣይ ወደ መጡበት ስመለሱ በየአካባቢያቸው ያለውን የልማት ፀጋዎችን በመለየት አምርታዊ ለውጥችን ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *