በቦንጋ ማዕከል “የህልም ጉልበት፤ለእመርታዊ ጉልበት “!በሚል መሪ ሀሳብ እየሰለጠኑ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የልማት ስራዎችን ጎበኙ

Spread the love

በካፋ ቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙትን የኮሪደር ልማት ፣ፍቅሩ የዶሮ እርባታ እና ብሔራዊ የቡና ሙዚየም የልማት ስራዎችን ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛል።

የመስክ ምልከታዉ ሠልጣኞች ከንድፈ ሀሳብ ባሻገር ከተግባር ተሞክሮና ከልምድ መማማር የሚያስችል ነው።

የኮሪደር ልማት ከተሞችን ለኑሮና ለስራ የተመቹ ዘመናዊ፤ ጽዱና ውብ ለማድረግ እየተደረገ ያለው ርብርብም ፓርቲያችን ዘመን በመዋጀት ረገድ ሊታበል የማይችል ፕሮጀክቶችን እየሠራ መሆኑ ማሳያ ነው።

የቦንጋ ከተማ የኮሪደር ልማት 7/24 ሰአትን በመስራት ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ለመኖር ምቹ ለማድረግ፣ ማደስ፤ ገጽታዋን በማሻሻል ረገድ የኮረደር ልማት ስራው እየተፋጠነ ይገኛል ፡

የቦንጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ቁጥር 1 ሁሉንም መሠረተ ልማቶችን በማስተሳሰር በመስክ ምልከተው ቅኝት የተደረገ ሲሆን ቀሪ የኮሪደር ልማት ስራዎች እንዳሉም ማብራሪያው ተሰጥቷል።

እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራት በርካታ ስራ አጥ ወጣቶችን በዘርፉ በመሰማራት ተጠቃሚ እያደረጋቸው ይገኛል።

እንደ ሀገር ለተጀመረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን ማሳለጥ የሚያስችል የዶሮ እርባታ ስራዎችን ሰልጣኞቹ ምልከታ አድርገዋል።

በአመራሩ ዘንድ የልምድ ልውውጥ መከናወኑ በየአካባቢው ተመሳሳይ ልማትን ለማምጣት አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑም አመራሮቹ ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *