





የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በክልሉ ውሰጥ ካሉ የግል ኮሌጆች ጋር የምክክር በታርጫ ከተማ መድረክ አካሂዷል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል እንደገለፁት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ዓላማው በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ በሥራ ገበያ ተወዳዳሪ፣ ብቁ፣ ሥራ ፈጣሪና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ዜጋ መፍጠር ነው።
በመሆኑም ገበያው የሚፈልገውን ብቃትና ተነሳሽነትን የተላበሰና ከሥራ ፍላጎት ጋር ራሱን የሚያስማማ አምራች መፍጠር ላይ እየተሠራ ይገኛል።
ቢሮው አሁን ላይ የሚሠሩ ብርቱ እጆችንና ብሩህ አእምሮ ባለቤቶችን የማዘጋጀት ተልዕኮ እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን የክልሉን አቅምና ፀጋን በመለየት የስልጠና ሂደቱ በተቀናጀ ጥረት እየተከናወነ እንዳለም ወይዘሮ ቤተልሔም ገልጸዋል።
ስለሆነም ከግል ኮሌጆች ጋር የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር፣ በመናበብና በመቀናጀት መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሥራ ትስስርና የተቀናጀ የአሰራር ማዕቀፍ ማጠናከር ተገቢ መሆኑም ተገልጿል።
በተለይም በኢንዱስትሪው የሙያ ደረጃ ምደባንና የሙያ ብቃት ምዘናን በባለቤትነት እንዲመራም ተጠይቋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፊ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አየለ በበኩላቸው ለሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቁ ስኬት ሀብት በመሆኑ ድጋፍና ክትትል ልደረግ እንደሚገባ አብራርተዋል።
ለወጣቶች የሥራ ዕድልን በማመቻቸት የተሻለ ነገን ለማየት በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላት ተናቦ መሰራት የጎላ ሚና አለው ብለዋል
በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ላይ ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ላይ የተዘጋጀ ሠነድ ቀርቦ ተወያይተውበታል።
ከግል ኮሌጆች ከተገኙ ተሳታፊዎች መካከል የዳይናሚክ ሆራይዝን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲን አቶ አበራ አድነው በበኩላቸው ሰልጣኞችን ከማደራጀትና ሀብት ከማመቻቸት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ጉድለቶች መኖራቸውን አንሰተዋል።
በእርሻ ዙርያ ለሰለጠኑ ማሽነሪዎችን በማመቻቸት ወደ ሥራ ቢገቡ ትርፋማ መሆናቸው አንሰተው ከሚመለከታቸው አካላተ ተገቢ ድጋፊ ሊደረግ ይገባልም ብለዋል።
አብሲኒያ ሻይን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲን አቶ ሙሉቀን ገዛኸኝ እንዳሉት በግል ኮሌጆች የሚገኙ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት እንዲሁም የመንግሥትና የግል ኮሌጅ በመናብብና በመቀናጀት የሚታዩ ማነቆችን በጋራ በማረምና በመገምገም የተሻለ ዜጋና ማፍራት እንደሚቻል ገልፀዋል
ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በምክክር መድረኩ የክልሉ ሙያና ምዘና ብቃት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቆጭቶ ማሞን ጨምሮ የኮሌጅ ባለቤቶች፣ ዲኖች የቢሮ ባለሙያዎች ተገኝተውበታል።
