ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-

Spread the love

👉 እንደ ሀገር በተለያዩ ተቋማት እና ዘርፎች ሪፎርም ሥንሠራ ቆይተናል፤ ከዚህ ዓመት ጀምሮ እንደ ሀገር የምናንሠራራበት ጊዜ ነው፡፡ በርካታ ውጤቶችም ይጠበቃሉ፡፡ ቀጣዩ የማጽናት ጊዜ ይሆናል፡፡

👉 አንዳንዶች ትፈርሳላችሁ ቢሉም፤ እንደማንፈርስ እንደ ሀገር በተግባር እያሳየን ነው፡፡ ይህ ጥንካሬ በይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

👉 ባለፈው ዓመት 8 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግበናል፤ ይህም እጅግ አበረታች እና ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሁሉ አስደማሚ ሆኗል፡፡

👉 በያዝነው ዓመት ደግሞ 8 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ በቅንጅት ርብርብ እያደረግን ነው፡፡

👉 የግብርናው ዘርፍ ብቻ በዚህ ዓመት 6 ነጥበ1 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ብለን እንጠብቃለን፤ ለዚህም አስፈላጊውን ሁሉ እያደረግን ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *