

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ይህ ዓመት ሪፎርሞቻችንን ጨርሰን በታሪካችን አይተን የማናውቃቸውን ውጤቶች እያየን ለትውልድ የማንፅናት ሥራ የምንጀምርበት ዘመን መጀመሪያ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከሕዘዝብ እንደራሴዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
ባለፉት ስድስት ዓመታት በሀገሪቱ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ሪፎርም ሲካሄድ መቆየቱን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሪፎርም ሥራዎች ቀሪ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሪፎርሙ ያልነካው ዘርፍ የለም ብለዋል፡፡ የተሠሩት ሪፎርሞችም በርካታ ትምህርቶች የተቀሰሙባቸው ናቸው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ይህ ዓመት ሪፎርሞቻችንን ጨርሰን ሀገራዊ ማንሠራራት የምንጀምርበትና በታሪካችን አይተን የማናውቃቸውን ውጤቶች እያየን ለትውልድ የማንፅናት ሥራ የምንጀምርበት ዘመን መጀመሪያ ነው ሲሉም ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡
