የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደቱ ግለፀኝነትና አሳታፊ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ገለፁ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እየተከናወነ ያለውን 3ኛ ቀኑን የያዘውን የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ አስመልክቶ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቦንጋ ከተማ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ የእስካሁን ያለውን የምክክሩን ሂደት ከሁሉም ወረዳዎች የተመረጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች ግልጽና አሳታፊ በሆነ መልኩ አጀንዳቸውን አደራጅተው ያጠናቀቁበት የምክክር መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ የህብረተሰብ ወኪሎች ጋር የተደረገው ያለፉት የሶስት ቀናት የምክክር መድረክ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተሳታፊዎች አጀንዳቸውን በማቅረብና በመፈራረም፣ በቀጣዮቹ ቀናት ለሚደረጉት የምክክር ሂደቶች ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ሂደቱም በታቀደው መልኩ በስኬት መጠናቀቁንም አክለዋል።

ከነገ ጀምሮ በሚኖሩ ቀጣዮቹ ቀናት ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የባለድርሻ አካላት ምክክር መድረክ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።

በክልሉ እየተካሄደ ያለው የምክክር መድረክ እንዲሳካ አስተዋፅኦ እያደረጉ ላደረጉ አካላትም ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ አመስግነዋል።

ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ ከህዝብ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት የተቻለውን ሁሉ እየተወጣ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

በዚህም ሂደት ኮሚሽኑ ከህብረተሰቡ የሚነሱ አጀንዳዎች ውሳኔ እንዲሰጥበት አበክሮ እንደሚሰራ አስረድተዋል።

የምክክር ሂደቱ ውጤታማ ለማድረግና ችግሮቹን ለመፍታት ውይይት፣ በመመካከር እና የመደማመጥ ባህልን መሠረት በማድረግ በአስፈላጊውን ጥረት ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው አብራርተዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በቀጣይ ቀናት በሚኖራው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ላይ ሁሉም የባለድርሻ አካላት ወኪሎች የአጀንዳዎቹ አስፈላጊነት በመገንዘብ በንቃት እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *