





የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የባህል ፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ የተመራ የፌዴራል፣ የክልልና የተለያዩ ሚዲያ አካላት ልዑካን በካፋ ዞን ጉርጉቶ የእግዜር ድልድይ የቦንጋ ብሔራዊ የቡና ሙዝዬም ጎብኝተዋል።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ነጋሽ በጉብኝቱ በዩትና በሰሙት በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው በዚህ ቦታ የተገኝንበት ዋና አላማ የዓለም የቱሪዝም ቀንን ምክንያቱ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ተልዕኮ ለዘርፉ የሰው ሃይል በማሰልጠን ብቃት ያለው ባለሙያ በማፍራት ጥናትና ምርምር በማካሄድ ዘርፉን ማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት ነው ያሉት፡፡
በትላንትናው ዕለት በክልሉ ምን አይነት የቱሪዝም ሀብቶች እንዳሉና ቱሪስት ብመጣ ምን ነገሮች መጎብኘት ይችላል በሚል የቱሪስት ጋይድና ሌሎች ነገሮችን የያዘ ጥናት በማስጠናት ለክልሉ ማስረከቡን አንስተው ዛሬ ያየነው የቱሪዝም ፀጋ ተፈጥሯዊና ባህላዊም ይሁኑ ሰው ሰራሽ ለአመታት ከእኛ ጋር የኖሩና አሁን ባለንበት ሁኔታ የሁሉም ማህበረሰብ አይን ተከፍቶ የቱሪዝም ሀብቶችን ከመጠበቅ ወደ መጠቀም እየተሸጋገረን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ያሉ ታርካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪዝም ሀብቶች መጠበቅ፣ለትውልድ መተላለፍ እና መጠቀም መቻል እንደለበትም ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው አሳስበዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ በበኩላቸው፣ የቦንጋ ብሔራዊ የቡና ሙዝዬም ከቡናና ከካፋ ህዝቦች ጋር ቁርኝት ያለው ታሪካዊና ገላጭ ሙዝዬም መሆኑን አንስተዋል፡፡
የክልላችን ከሚገኙ በርካታ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች መካከል በተቀናጀ እና በተደራጀ መንገድ ተጠብቆ ያለው ይህ የቦንጋ ብሔራዊ የቡና ሙዝዬም ለክልሉ ግንባር ቀደም የቱሪዝም መዳረሻ ነው ብለዋል፡፡
በክልላችን ያሉ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በማልማት ለትዉልድ ማስተላለፍ ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለበት መሆኑን የገለጹት አቶ ፋንታሁን የቱሪዝም ሀብቶችን በተሻለ መንገድ በማልማት፣ መጠቀምና በማስተዋወቅ የኢኮኖሚ ምንጭ ማድረግ እንደሚገባ ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት አጽንኦት ሰጥተዉ መስራት አለባቸው ሲሉም ተደምጠዋል።
በቦንጋ ብሔራዊ የቡና ሙዝዬም ጉብኝት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕረዝዳንት ዶክተር ከለለው አዲሱ እንደ ሀገር መንግሥት ትኩረት ከሰጠቻቸው ዘርፎች የቱሪዝም አንዱ መሆኑን ገልጻው በተለይ የዘንድሮው የቱሪዝም በዓል ቱሪዝም ለሠላም በምል መሪ ቃል መከበሩ ቱሪዝም ለሠላም እና ለብልፅግና ብሎም ለህዝቦች ትስስር ያለውን አስተዋጽኦ አመላካች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ጉብኝቱ ላይ የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ነጋሽን ጨምሮ የክልሉ የባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ እና ሌሎች የክልሉና የዞን እንዲሁም የተለያዩ የሚዲያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
