ኢትዮጵያን ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ

Spread the love

ኢትዮጵያን ተመራጭ የጎብኚ መዳረሻ ለማድረግ በሚከናወነው ሥራ የቱሪስት እና የኮንፈረንስ ቪዛዎች ላይ እስከ 25 በመቶ ቅናሽ መደረጉ የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተመላከተ፡፡

የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለማበረታታት በ2016 ዓ.ም በፀደቀው የኢሚግሬሽን ደንብ ቁጥር 550/2016 የአገልግሎት ዋጋ ተመን የዋጋ ቅናሽ መደረጉን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ማስተዋል ገዳ አስታውሰዋል፡፡

በዚህም የቱሪስት ቪዛ ከዚህ በፊት ከነበረው 25 በመቶ ቅናሽ በማድረግ ኢትዮጵያ በዓለም የቱሪዝም መዳረሻ ተመራጭ እንድትሆን እየተደረገ ባለው ጥረት የበኩሉን ሚና እያበረከተ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያን የዓለማችን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማእከል ለማድረግ የኮንፈረንስ ቪዛ ክፍያ ከዚህ በፊት ከነበረው ተመን በ23 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያን ተመራጭ የጎብኚ መዳረሻ ለማድረግ በሚከናወነው ሥራ ከላይ የተገለጹት ማሻሻያዎች የራሳቸውን ሚና እያበረከቱ መሆኑን አመላክተዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *