



በምዕራብ ኦሞ ዞን የ2016 የበጋው መስኖ ስንዴ እቅድ አፈጻጸም እና የ2017 እቅድ እንዲሁም በልማት ትሩፋት ሥራዎች ዙሪያ ዉይይት እየተደረገ ይገኛል።
በመድረክ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ጌታቸዉ ኬኒ እንደተናገሩት የበጋ መስኖ ስንዴ የልማት ሥራዎች ከአምናው በነበረው ልምዶች በዘንድሮው የተሻለ ምርት ለማግኘት መትጋት ይጠበቃል ብልዋል።
አያይዘውም በ2016ዓም 488ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ መሸፈኑ የገለፁት ዋና አስተዳደሪ ይህ ተግባር ይበልጥ ዉጤታማ ለማድረግ በየደረጃው ያሉት አካላት ልዩ ትኩረት መስጠት ይጠበቃል ብልዋል።
አያይዘውም የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት በህብረተሰቡ ላይ የግንዛቤ ሥራዎች በመስራት ባላቸው መሬት የሌማት ትሩፋት ሥራዎች መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በድሉ መዓዛ እንደተናገሩት የበጋ መስኖ ስንዴ በሀገር ደረጃ ልዩ ትኩረት ተሰጠው እየተሰራ ያለው በመሆኑ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቃል ብልዋል።
የኑሮ ውድነት ልቀርፍ የሚችለው መስራት እና መስራት ብቻ በመሆኑ የተናገሩት አቶ በድሉ የልማት ትሩፋት በየመንደሩ በአግባቡ መስራት ይጠበቃል ነው ያሉት።
የዞኑ ግብርና እና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ሃላፊ አቶ መልኬ ኬላጌ በበኩላቸው ያሉን የዉሃ አማራጮች በአግባቡ በመጠቀም የበጋ መስኖ እና መደበኛ መስኖ ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባ ተናግሯል።
አክለው በ2016 ዓም 488ሄክታር መሬት ማልማት መቻላቸውን አውስተው በአልም ባለሀብቶች 35 ሄክታር በአርሶ አደሮች 453በሄክታር እንዲያለሙ መደረጉ ገልጸዋል።
በዘንድሮው 2017ዓም ከ1ሺህ 753 ሄክታር በላይ ለማልማት እና ከ61ሺህ 355 ኩንታል ምርት ለማግኘት ትኩረት ተሰጠው እየተሰራ መሆኑ አቶ መልኬ አስገንዝበዋል።
በመድረኩ እቅድ እና አፈጻጸም ያቀረቡት የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ ማናዬ ማሞ እንደተናገሩት ከበጋዉ መስኖ ስንዴ ጎን ለጎን የመደበኛ መስኖ የአትክልት እና የስራስር ሰብሎች ማልማት ይጠበቃል ብልዋል።
አቶ ማናዬ አያይዘውም በዘንድሮው በመደበኛ መስኖ በሆሊቲካልቸር ሰብሎች ላይ ከ2ሺህ 380 ሄክታር መሬት በማልማት እና ከ356ሺህ 850 ኩንታል ምርት ለማግኘት ግብ ተይዘው እየተሰራ መሆኑ አስገንዝበዋል።
በመድረኩ የዞን የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል።
