የህገመንግሰት እና ለፌራልዝም አስተሳሰብ እንዲጎለብት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል፦ አቶ መቱ አኩ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 19ኛው የኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ህብረ ብሔራዊ የፌዴራልዝም ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሀሳቦች ላይ ለባለድርሻ አካላት በቦንጋ ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል።

የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መቱ አኩ በስልጠናው መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የስልጠናው ዋና ዓላማ ህብረ ብሔራዊ ፌዴራልዝም ሥርዓት እንዲጎለብትና ስር እንዲሰድ ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል።

በበዓሉ ላይ የህገመንግሰት እና ለፌራልዝም አስተሳሰብ እንዲጎለብት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አቶ መቱ ገልፀዋል።

አቶ መቱ አክለውም የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተለያዩ እርከኖች በፌዴራልዝም አስተምህሮት እና አተገባበር ላይ ስልጠና መስጠቱንና እንደ ክልል በቀጣይ ይህንን የፌዴራልዝም አስተምህሮት ግንዛቤ እየፈጠርንና እያጠናከረን የሚንሄድበት ነው ብለዋል።

በበዓሉ አከባበር ላይ የሚዲያ አጠቃቀምን ከወትሮው በተሻለ መንገድ ተግባራዊ በማድረግ በዓሉን ለመክበር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

የብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ መሰለ ከበደ በበኩላቸው ህገ መንግስት ኖሮ ህገመንግስታዊነት ያለመኖር ትርጉም የሌላው በመሆኑ በዚህም የሚታዩ ክፍታቶችን ለማረም ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ የመፍጠር ስራ መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

በክልሉ ህገመንግስትና የፌዴራልዝም አስተምህሮት ስራ እናሰፋለን ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤው ለዚህም ባለፈው ዓመት የተወሰኑ ተግባራት መከናወናቸውንና በቀጣይ በ13ቱም ብሔረሰቦች አፍ መፍቻ ቋንቋ የአስተምሮ ስራ ለመስራት መታቀዱን ጠቁመዋል፡፡

በስልጠናው ህብረ ብሔራዊ የፌዴራልዝም ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሀሳቦች ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ማብራሪያ የተደረገበት ሲሆን ውይይትም ተደርጎበታል።

የመድረኩ ተሳታፊዎቹ በፌዴራልዝም ሥርዓት ፣ ተግዳሮቶች እና የመፍትሔ ሀሳቦች ዙሪያ የቀረቡ ሰነዶች በታች መዋቅር በአተገባበር ሂደቱ ላይ የሚፈጠሩ ብዥታዎችን ለመቅረፍ ጥሩ ይዘቶች ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፌዴራልዝም ስርዓት አስተምህሮት ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ተግባር ከዘመቻ ባለፈ ቀጣይነት ባለው መልኩ ታቅዶ መሰራት ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃልከህዳር 25 እስከ 29 በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *