



በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ፣በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ እንዲሁም በክልላችን ለ3ኛ ጊዜ የጸረ _ሙስና ቀን በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።
በዓሉ “ወጣቶችን ያማከለ የጸረ_ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነዘባል ” በሚል መሪ ቃል በሚዛን አማን ከተማ በመከበር ላይ ነው ።
በዓሉን በማስመልከትም ንግግር ያደረጉት የክልሉ ስነ_ምግባርና ጸረ_ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ የበዓሉ መከበር አስተሳሰቦቻችን ሙስናን በወሳኝ መልኩ ሊያርም በሚችል ወጣቱን ባለቤት በማድረግ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ቀኑ በሁሉም መልክ ሙስናን ለመዋጋት እና በህብረተሰቡ ውስጥ ታማኝነትን ለማጎልበት ያለን የጋራ ኃላፊነት ጠንካራ ማስታወሻ ሆኖ ያገልግላል ሲሉም ኮሚሽነር ሙሉሰው ተናግረዋል ።
ሙስና የፖለቲካ ወይም የኢኮኖሚ ጉዳይ ብቻ አይደለም፣በሁሉም የህይወታችን ዘርፎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር የሞራል ፈተና ነው ሲሉም ኮሚሽነር ሙሉሰው ተናግረዋል ።
ዛሬ እዚህ በምንሰበሰብበት ወቅት እያንዳንዳችሁ በተለይም ወጣቶች አቅማችሁን እንደ የለውጥ ፈላጊዎች እንድትገነዝቡ እጠይቃለሁ ሲሉ ገልጸዋል።
በትምህርትና በአስተዳደር ሂደቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ እኩዮቻችሁንና ማህበረሰቡ ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ የማድረግ ችሎታ አላችሁ፤ ሙስናን በጋራ በመቆም፣ታማኝነት ከምንም በላይ የሚከበርበትን የወደፊት ጊዜ ለመቅረጽ መርዳት ትችላላችሁ ሲሉም ኮሚሽነር ሙሉ ሰው ዘውዴ ለወጣቶች መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ሙስና በጉቦ፣ገንዘብ በማጭበርበር ፣ወገንተኝነት እና ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም ከመገለጫዎቹ ጥቂቶች መሆናቸውን ያስታወሱት ኮሚሽነር ሙሉሰው እነዚህ ተግባራት ተቋማትን ያዳክማል ፣የኢኮኖሚ ልማትን ያቀዘቅዛል፣ለመንግስታዊ አለመረጋጋት አስተዋጽኦ ያደርጋል፣በህብረተሰቡ ውስጥ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን እንደሚጎዳም ገልጸዋል።
ሙስናን ለመዋጋት በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መስራትን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ኃላፊነት ለሚሰማው ዜግነት ማዘጋጀት አለባቸው ብለዋል።
የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች ማህበረሰቡን በስነምግባር አስተምህሮዎች ላይ የተመሰረተ ታማኝነትና ሙስና የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በመረዳት ትውልዱ ላይ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የጸረሙስና ቀን በተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎች ፣ በስ_ነግጥም ፣ በድራማ፣በተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር እየተከበረ ሲሆን ዕለቱን የተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።
የክልሉ ስነ_ምግባርና ጸረ_ሙስና ኮሚሽን በቴክኖሎጂ የታገዘ ዌብሳይት አልምቶ ስራ ላይ ማዋሉንም በዕለቱ ገለጻና ማብራሪያ በአቶ ሙባረክ አበበ ቀርቧል።
በበዓሉ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የዞን አመራሮች፣የሀገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት አባቶች፣የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ቡድን አስተባባሪዎች፣ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በታጠቅ አበበ
