



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል
የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ብልጽግና ፓርቲ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችል ፍኖተ ብልጽግና በማዘጋጀት ከዚህም የተቀዳ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ በመንደፍ ፍርጀ ብዙ ተግባራትን በማከናወን በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል ።እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል።
የክልሉ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሀገራዊ አቅጣጫ የተቀዳና የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ በማቀድ መላውን አመራር፣አባልና ደጋፊዎችን በማስተባበር በርካታ ስራዎችን በመስረት ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።
በብልጽግና እሳቤዎች ቅኝት በክልሉ ባለፉት ወራት በሁሉም የፓርቲ ስራዎች ውጤታማ የተግባር አፈፃፀም መከናወን መቻሉን አመላክተዋል።
በዚህም የፓርቲው መዋቅሮች ህልማቸውን በብቃት መወጣት እንዲችለ የአመራር ምዘና ፣ግምገማና አመራርን መልሶ የማደራጀት ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።
እንደ ሀገርና ክልል የመፈጸም፣ የማስፈጸምና የማስተባበር አቅም ማደጉ የታየበት በተለይም የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ስልጠና ፓርቲው በአቅም ግንባታ ዘርፍ ያለውን ልምድ እያጠናከረ መሆኑን ያሳየበት መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በአመራሩና አባሉ ዘንድ ለቀጣይ ተልዕኮ ስንቅ የተያዘበትና አዲስ የተነሳሽነት ስሜት የተፈጠረበት ትልቅ መድረክ እንደነበር ጠቁመዋል።
በፓርቲ መሪነት የሚከናወኑት የንቅናቄ አጀንዳዎች በስኬታማነት የመምራት ሚናችንን እየተወጣን እንገኛለን ብለዋል።
አቶ ነጋ አክለውም አዎንታዊ ሰለም ሊፈጥሩ የሚችሉ ስራዎችን ማጠናከር፣ከተረጅነት የመላቀቅ ስራዎችና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የሆኑት የመንግስት አገልግሎትን ላይ በልዩ ትኩረት በተናበበ መልኩ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የእስካሁኑ ስኬቶችን አስጠብቆ ለማስፋት፣ክፍተቶችን ለመሙላትና መጪውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ በውጤታማነት የታጀበ የህዝብ ንቅናቄ ስራዎች በላቀ ቁርጠኝነት በመፈጸምና በማስፈጸም የብልጽግና ህልሞችን ለማሳካት ርብርብ መድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
ከዕቅድ አፈጻጸሙ ጎን ለጎን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በየዞኖች በወረዳና በከተማ አስተዳደር ያደረገውን ድጋፍና ክትትል የመስክ ምልከታ ሪፖርት ይቀርባል።
በመድረኩ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ፣የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ፣ የፓርቲው ጽ/ቤት አመራሮች ፣ የክልል ማዕከል መሠረታዊ ድርጅት አመራሮች ፣የዞን፣ የወረዳና ከተማ አስተዳር አመራሮች ተገኝተዋል።
