የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሳምንት የተመለከቱ ሁነቶች በአዲስ አበባ እየተካሄዱ ነው

Spread the love

የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሳምንት የተመለከቱ ሁነቶች በአፍሪካ ሕብረት ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

“የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ አረንጓዴ ኢንዱስትሪ እና የአዕምሯዊ ንብረትን አቅሞች በመጠቀም የአፍሪካን ትራንስፎርሜሽን እውን ማድረግ” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እየተከናወነ ነው።

ውይይቱ የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ምህዳር እየገጠሙት ያሉ አብይት ፈተናዎች እና መፍትሔዎቻቸው ያተኮረ መሆኑን ኢዜአ ከአፍሪካ ሕብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተያያዘም የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሳምንት አካል የሆነው ሶስተኛው በአፍሪካ አምራች በማቀነባበር ስራ የተሰማሩ ሴቶች ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል።

ውይይቱ “የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና የፈጠራቸውን እድሎች መጠቀም፤ በብልጽግና ጎዳና መጓዝ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከናወን መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት አስታውቋል።

በውይይቶች የአፍሪካ ሕብረት የስራ ኃላፊዎች፣ የኢንዱስትሪ ልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች እንዲሁም የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሳምንት የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማጠናከርና ለኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች እና ዲጂታል መሰረተ ልማቶች የሚያስፈልጉ አማራጭ የፋይናንስ አማራጮችን በመፈለግ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጉዞን መደገፍ የሚያስችሉ ውይይቶች እንደሚካሄዱ ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *