ከደቡብ ሱዳን ተነስተዉ በሱርማ ወረዳ ከብት ለመዝረፍ የሞከሩ አርብቶአደሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Spread the love

ከደቡብ ሱዳን መነሻቸዉን አድርገዉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚገኘዉ ምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ የአርብቶ አደሮችን ከብቶችን ዘርፈዉ ለመሄድ የሞከሩ 46 የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ

የኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣የፌዴራል ፖሊስ እና የክልልና የአካባቢዉ ፖሊስ በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉን የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ገልጸዋል::

የተዘረፉ 250 ከብቶች እና 21 የተለያዩ ጦር መሳሪያዎች መያዛቸዉን ኃላፊዉ አመልክተዋል።

የተመለሱ ከብቶች ለባለቤቶች የተሰጡ ሲሆን ዘራፊዎቹ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ አቶ አንድነት አሸናፊ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *