


ከደቡብ ሱዳን መነሻቸዉን አድርገዉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚገኘዉ ምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ የአርብቶ አደሮችን ከብቶችን ዘርፈዉ ለመሄድ የሞከሩ 46 የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ
የኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣የፌዴራል ፖሊስ እና የክልልና የአካባቢዉ ፖሊስ በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉን የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ገልጸዋል::
የተዘረፉ 250 ከብቶች እና 21 የተለያዩ ጦር መሳሪያዎች መያዛቸዉን ኃላፊዉ አመልክተዋል።
የተመለሱ ከብቶች ለባለቤቶች የተሰጡ ሲሆን ዘራፊዎቹ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ አቶ አንድነት አሸናፊ ገልጸዋል።
