ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መርቀው ከፈቱ

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እየተገነቡ ካሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተጓዳኝ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወዳጅ በሆኑት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሸኽ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ድጋፍ የተገነባው ማዕከሉ ወላጅ የሌላቸውን እና በችግር ውስጥ ያሉ ህጻናትን ከማሳደግ ባሻገር የሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ትብብር ማሳያ እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

One thought on “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መርቀው ከፈቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *