የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ ከፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለዳዉሮና ኮንታ ገቢዎች መምሪያ ለሚገኙ ባለሙያዎች ሥልጠና እየሰጠ ነዉ

Spread the love

በሥልጠናው የተገኙ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የደንበኛ አገልግሎት የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንዱ ታደሰ እንደተናገሩት ከየካቲት 1 ጀምሮ በክልሉ ሁሉም የገቢ ሰብሳቢ ተቋማት በአንድ የአሠራር ሥርዓት በመታገዝ ወጥ አካሄድ እንዲኖር ይሠራል ብለዋል።

በቀጣይም በQR CODE የተመዘገበና የተረጋገጠ የማኑዋል ደረሰኝ በኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ የሚተካ ይሆናልም ስሉ ገልጸዋል።

ከታህሣሥ 30 ጀምሮ የታክስ ሪፖርት ከየተቋማቱ በማኑዋል የማይቀርብ ሲሆን በE_tax ሥርዓት ከያሉበት የሚያቀርቡ መሆኑን አመልክተዋል።

ይህ ሂደት በቀጣይ ከግል ድርጅቶች ጋር የነበረውን የመረጃ ልውውጥ ሥርዓትንም ተጠቃሚ ያደርጋል ያሉት አቶ ወንዱ በበጀት ዓመቱ በደረሰኝ ከሚሰበሰበው ገቢ ከ10 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እንዲቻል ግብ ተጥሎ እየተሠራ በመሆኑ በደረሰኝ አሰባሰብ ላይ በሚፈጠረው ችግር ሕገወጦች ያልተገባ ጥቅም እንዳያገኙ በተቀናጀ ርብርብ ሊሠራ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በደረሰኝ ገቢን በተገቢው መሰብሰብ ከንግድ ትርፍና ከጋራ ገቢ ማግኘት የሚቻለውን እንደሚያግዝ ነው የተገለጸው።

በፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ መረጀና ሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ቡድን አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ይልማ በበኩላቸው የፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር ክልሎችን በመደገፍ የዘርፉን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

ስለሆነም በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ጠቃሜታ ያለውን ዓላማን በማንገብ ፍትሃዊና ዘመናዊ የግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ሥርዓት በማስፈን ጥራት ያለውን መረጃ በማደራጀት ተግባራትን በተገቢው ማከናወን ይገባቸዋል ብለዋል።

ደረሰኝ የማይኖር ከሆነ ገቢ እንደማይኖር ታሳቢ በማድረግ በገቢ ዘርፍ የሚከናወን ተግባር በትኩረት ሊከናወንም ይገባል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *