



በቀጣይም 8700 ኩንታል ለስትራቴጂክ የምግብ ሰብል መጠባበቂያ ክምችት ከ240 ሄክታር በላይ መሬት ላይ እንደሚመረትም በንቅናቄ መድረኩ ተገልጿል።
የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት እንደ ሀገር ተረጂነትን ማስቀረት የሀገር ሉአላዊነትና ክብርን ማስጠበቅ ነው ብለዋል።
መንግስትም ተረጂነትና ልመናን የሚፈፀየፍ ትውልድና ሀገር ለመፍጠር በገጠርና በከተማ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን እየፈፀመ ይገኛል ብለዋል።
እንደ ዞንም ተረጂነትና ልመናን ታሪክ ለማድረግ በርካታ ኢንሼቲቮች ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው የሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም መፈጸም የሚቻልበትና የምግብ ዋስትናችንን ማረጋገጥ ቁልፍ ተግባር ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አመራሩ የተግባሩ የትኩረት ማዕከል ሆኖ እንደሚሰራም ኃላፊው ገልጸዋል።
የዞኑ ግብርና ፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ ዞናዊ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የንቅናቄ ሰነዱን ሲያቀርቡ እንደተናገሩት ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ምንም እንኳ እንደ ዞን ስር የሰደደ የምግብ ዋስትና ችግር ባይኖርም የአደጋ ስጋት አዝማሚያዎችን መሰረት በማድረግ ዞናዊ ስትራቴጂክ የምግብ እህል ክምችት ማከናወንና የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል። በተለይም በከተሞች የሚታየውን የምግብ ዋስትና ችግርና ልመናን ማስቀረት ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የተሳተፉ አመራሮች እንደተናገሩት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ቁልፍ ተግባር በመሆን ወደ ታች ወስዶ መተግበር ይገባል ብለዋል።
የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን በመድረኩ ማጠቃለያ እንደተናገሩት ተግባሩ ሳይንጠባጠብ እንዲሰራና በውጤት እንዲታጀብ የአመራሩ የቅርብ ድጋፍና ክትትል እንዲሁም የግብርና ባለሙያው ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
እርሻው ቢቻል በኩታ ገጠምና በቅንጅት ቢሰራ መልካም ነው ያሉት ኃላፊው የተለዩ መሬቶችም በጋይድ ማፕ ተለይተው ሊቀመጡ ይገባል ማለታቸዉን የቤንች ሸኮ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል።
