







የኢፌዲሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ገብተው የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።
በወረዳዉ ዮኪጭጭ ቀበሌ በሴቶች አደረጃጀት እየተከናወኑ የሚገኙ የማር መንደርን ጎብኝተዋል።
ማህበሩ 78 ዘመናዊ የንብ ቀፎ ያሉት ሲሆን በዓመት 500 ኪ.ግ ማር እንደሚያገኙ፣ማርን ከማምረት ባለፈ በግ፣ፍየል፣በሬ እንደሚያደልቡ፣የበጋ መስኖ ስንዴን በማምረት ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል።
በ2016 ምርት ዘመን 1.5 ሄክታር መሬት ማሳ ላይ የበጋ መስኖ ስንዴ በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸው ገልፀው የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ማህበራቸውን እንደሚያጠናክሩና ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውንም በጉብኝቱ ወቅት ለማወቅ ተችሏል።
በተጨማሪም በወረዳው ዮክጭጭ ቀበሌ የሞዴል አርሶአደር ገቢቶ ሾደኖ 4ሄክታር የእንሰት ማሳም በሚኒስትሩ ተጎብኝቷል።
1 እንሰት በቁሙ ከ1200 እስከ 1500 ብር እንደሚሸጡ የተናገሩት ሞዴል አርሶአደር ገቢቶ ሾደኖ ተፍቆ ከተሸጠ ከ3ሺህ በላይ እንደሆነ ገልፀዋል።
ባዩት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ መሠል ተግባራት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተሞክሮ ልሠፋ ይገባል ብለዋል።
የሌማት ትሩፋትን ምንነት በተገቢው ተረድቶ በተግባር ያሳየ አካባቢ መሆኑንም አክለዋል ሚኒስትሩ።
የሞዴል አርሶ አደር ከበደ ገሊቶ የንብ መንደር ፣የእንሰት ማሳ፣የበግና ፍየል እርባታ ጉብኝት የተደረገ ሲሆን ከማር ሽያጭ በሚያገኘው ገቢ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል አርሶ አደሩ።
በጉብኝቱ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
