






”የትምህርት ጥራት እምርታ ለሁለንተናዊ ብልጽግና!” በሚል መር ቃል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጰያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው 1ኛ ዙር የትምህርት ሴክተር ጉባኤ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ የ1ኛ ዙር የትምህርት ሴክተር ጉባኤ ክልላዊ የትምህርት ልማት ሥራዎች፣ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድም ተገልጿል።
በጉባኤው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታን ጨምሮ ክፍተኛ የክልሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ከክልሉ ስድስቱም ዞኖች የተገኙ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
በዕድገቱ በዛብህ
