



ኢትዮጵያን በማወቅ ለሌላው ዓለም በማስተዋወቅ የሀገሪቱን በጎ ገጽታ መገንባት እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ ኢትዮጵያ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወራረሱ የቆዩ አኩሪ ታሪካዊ ሐብቶች ያሏት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል፡፡
በመጪው የካቲት ወር በአዲስ አበባ በሚካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ስልጠናዎችን የወሰዱ ካዴቶች ብሔራዊ ቤተ-መንግስትን፣ አንድነት ፓርክን፣ የሳይንስ ሙዚየምን እና የወዳጅነት ፓርክን ጎብኝተዋል።
ካዴቶቹ እኚህን ታሪኮች ጠንቅቆ በማወቅ ለኢትዮጵያ በጎ ገጽታ ግንባታ ሊጠቀሙበት እንደሚገባም አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አስገንዝበዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉ በጎ ፈቃደኛ ካዴቶች በበኩላቸው የጎበኟቸው ሥፍራዎች ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ እና ቅርስ አዲስ ግንዛቤን እንደፈጠሩላቸው አስታውቀዋል፡፡
የሀገራቸው አምባሳደር በመሆን በሚሰማሩባቸው ተልዕኮዎች የኢትዮጵያን ገጽታ እንደሚያስተዋውቁም መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
