





በከተማዉ ዘንድሮ በ2 ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ምገባ ኘሮግራም ለማስጀመር ሲሠራ ቆይቷል። በዚሁ መሠረት በሶሬ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ታርጫ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ አዳር በሚያጠኑ ተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ተጀምሯል።
የምገባ መርሃ ግብር ያስጀመሩት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማዉ ዘዉዴ በበኩላቸው ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምገባ ማስጀመር የተማሪዎችን መጠነ ማቋረጥን ለመቀነስና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱና ዋነኛ ጉዳይ መሆኑን በመግለፅ በቀሪ ትምህርት ቤቶች ላይም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መሳተፍ እንዳለበት በመናገር ኘሮግራሙን ለማገዝ የሃምሳ ሺህ (50ሺ) ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ።
የታርጫ ከተማ ከንቲባ አቶ ዳዊት ወንድሙ በበኩላቸው ሀገርንም ሆነ አከባቢውን ለማልማት የለማ ማህበረሰብ ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ በ2017 ትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ተናግሯል።
አቶ ዳዊት አክለውም ለትምህርት ቤቶች የበጀት ድጋፍ የማድረግ፣ አምባሳደር አመራሮችን መመደብ፣ ተግባር አፈፃፀምን ወርዶ ክትትልና ድጋፍ የማድረግ፣ የመ/ራን ጥቅማጥቅምን ማስከበርና ለሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የመሰጠት ሥራ በልዩ ሁኔታ እየተተገበረ መሆኑን በመግለፅ አሁን የተጀመረውን የተማሪዎች ምግባ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደረግ ጥሪውን አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም ለዚህ ሁሉ ስኬት የበኩሉን አስተዋጽኦ ላበረከቱት አካላትን ከንቲባዉ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የዘገበዉ የታርጫ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ነዉ።
