ከ110 ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ህገወጥ መድኃኒቶች ማስወገዱን የሸካ ዞን ጤና መምሪያ ገለፀ

Spread the love

መድኃኒቶች የተወገዱት በህገወጥ መድኃኒቶች አስወጋጅ ግብረኃይል አማይነት መሆኑም ተጠቁሟል።

ባለፉት ጊዜያት በግብረኃይሉ ከተያዙ መድኃኒቶች መካከል ከ110 ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ህገወጥ መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች በመሆናቸው ማስወገድ መቻሉ ተገልጿል።

በመንግስት ጤና ተቋማት ብቻ መገኘት ያለባቸውና የግል ጤና ተቋማት መያዝ የማይችሉት መድኃኒቶች ከተወገዱት ውስጥ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ህገወጥ መድኃኒትና የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ የተገኘባቸው የጤና ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱንም ከመምሪያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ከተያዙት መድኃኒቶች መካከል ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸውና በኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን የተመዘገበና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጠ በመሆናቸው በግብረኃይሉ ተረጋግጦ ለባለንብረቶቹ መመለሱን ማረጋገጥ ተችሏል።

ህገወጥ ተግባራትን ተከታትሎ እርምጃ ከመውሰድ አንፃር የተጀመረው ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ህብረተሰቡም ለህግ ማስከበር ስራው ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሸካ ዞን ጤና መምሪያ ጥሪውን አቅርቧል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *