የብሄረሰቦች ምክር ቤት ለአንድ አቅም ደካም ቤት ገንብተው አስረከበ

Spread the love

የክልሉ የብሄረሰቦች ምክር ቤት በምዕራብ ኦሞ ዞን በጀሙ ከተማ ለሚገኘው ለአንድ አቅም ደካም ቤት ገንብተው አስረክቧል።

የክልሉ የብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ እንደተናገሩት በክልሉ 3 ቤቶች ገንብቶ ማስረከባቸውን ጠቅሶ የተቸገሩ አቅመ ደካሞች መርዳት ባህል ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሰው ተኮር ፓርቲ የተለያዩ ኢንሼቲቭቦች ቀርጾ እየሰራ መሆን የገለፁት አፈጉባኤ አቅም ደካሞች ማጋዝ መደገፍ ከፈጣሪ ዘንድ ትልቅ ቦታ አለው ብልዋል።

በጀሙ ከተማ ባጌቼ ኤሊ መንደር የተሰራ 42 ቅጠል ቆርቆሮ ከአጠቃላይ ወጪዎች ከ255ሺህ ብር በላይ ወጪ መጭረሱን አክሎበታል።

በዛሬው የተገኙ አፈጉባኤ ፋራሽ ብርድ ልብስ እና ሌሎች ድጋፎችን ለአቅመ ደካማ አስረክበዋል።

በክልሉ የተጀመረዉን ለአቅመ ደካሞችና በተለያየ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ቤት ግንባታ ስራ ተሳታፊ በመሆን የብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ እና ምክትል አፈጉባኤ አቶ መሰለ እና የዞኑ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ብልልኝ ወልደሰንበት እና የከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በቦታዉ በመገኘት 42 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ሰርተዉ በመጠናቀቁ አስረክበዋል።

የቤት ግንባታው ተጠቃሚ የሆኑት አቶ ማጣ እና ባለቤታቸዉ እንደተናገሩት ከዚህ በፊት በትንሽዬ ደሳሳ ጎጆ ቤት ዉስጥ በተለይ በዝናብ ጊዜ በብርድ ከእነ ልጆቻቸው ጋር በስቃይ ይኖሩ እንደነበር ተናገግረው ቢሮው ላደረገላቸው ድጋፍ ሁሉ አመስግነዋል ሲል የምዕራብ ኦሞ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *