ነገ በክልላችን የሚጀመረዉ የተቀናጀ የተፋስሰ ልማት ሥራ ህብረሰቡ በንቃት አንዲሳተፍ አቶ ማስረሻ በላቸዉ ጥሪ አቀረቡ

Spread the love

የ2017 የማህበረሰብ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት በክልላችን “የአፈር ሀብታችን ለብልጽግናችን”በሚል መሪ ቃል በጥር 22/2017 ዓ.ም ይጀመራል ያሉት የክልላችን ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ የተፈጥሮ ሀብት መመናመን እና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የዘንድሮው 2017 ዓ.ም የተቀናጀ የማህበረሰብ ተፋሰስ ልማት የተፈጥሮ ሀብት የመሬት ፣ የውሃና የሰው ሀብታችንን መጠበቅ ፣ ማልማትና በላቀ ደረጃ በማቀናጀት ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

የተፋሰስ ልማት ስራው ለተከታታይ 45 ቀናት ይካሄዳል ያሉት አቶ ማስረሻ ለዚህም አስፈላጊዉን ቅድሜ ዝግጅት ስራዎች ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ የተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል። ።

ለዘንድሮው የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ሥልጠና መስጠት፣የልየታና የዲዛይን ስራ እንዲሁም የሰዉ ኃይልም ይሁን የመሳሪያ ልየታ በተገቢዉ መከናወኑንም አመልክተዋል።

ከአሁን ቀደም በተሰራዉ ሥራ አመርቂ ዉጤት መገኙትን ያመላከቱት ኃላፊዉ ዘንድሮ 225 ሺህ ሄ/ መሬት ለማልማት መታቀዱን ገልጸዋል።

ሁልጊዜም ቢሆን በሁሉም የልማት ጥሪዎች የሚበረታታ የህብረተሰብ ተሳትፎ እንዳለ ያነሱት ኃላፊዉ በዘንድሮ ከ 1 ሚሊየን በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችም እንደሚሳተፉ አቶ ማስረሻ አብራርተዋል ።

በነገ ዕለት በክልላችን ባሉ ሁሉም ዞኖች በሚገኙ በ38 ወረዳዎች በይፋ የሚጀመርና ቀጣይነት ባለዉ መልኩ በንቅናቄ የሚመራ ስራ እንደሆነ የጠቁሙት ኃላፊዉ የክልላችን ህዝብም በዚህ ንቅናቄ ስራ በንቃት እንዲሳተፍ አቶ ማስረሻ በላቸዉ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *