የክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ – ሙስና ኮሚሽን በሃብት ማሳወቅና ምዝገባ ሂደት ላይ ለካፋ ዞን ማዕከል የመንግስት ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስነ-ምግባርና ፀረ – ሙስና ኮሚሽን ከአስር ቀን በኋላ ተግባራዊ የሚደረገውን የሃብት ማሳወቅና ምዝገባ ሂደት አስመልክቶ ከካፋ ዞን ማዕከል ለተወጣጡ መንግስት ሰራተኞች በቦንጋ ከተማ የግንዛቤ ስልጠና ሰጥቷል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳግም ዳንኤል ሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ በመንግስት ተቋማት፡ በመንግስት የልማት ድርጅቶችና በህዝባዊ ድርጅቶች መካከል መልካም ስነ-ምግባርና እሴተቶች እንድጎለብቱ ከማድረግ ባሻገር ተቋማዊ አቅምን በመንግባት የመንግስትና የህዝብ ሥራዎች አሠራር ግልፀኝነት እንድኖራቸው ያደርጋል ብለዋል።

የሥነ -ምግባር ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ዓለማና ተግባር የተሿሚዎችንና ሕጉ ግዴታ የጣለባቸዉ የመንግሥት ሠራተኞች እና የመንግስት ልማት ድርጅት ሠራተኞች ሀብትና የገቢ ምንጫቸዉን አሳወቀው እንድያስመዘግቡ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መዘጋጀቱ ትክክለኛ መረጃ ለዜጎች በማድረስ ሃብታቸውን እንያሳውቁና እንድያስመዘግቡ ለማስቻል እንደሆነም ተናግረዋል።

በየተቋማት የሚገኙ ሠራተኞች በሥነ-ምግባርና በመልካም እሴት ተገንብተው ተገልጋዮቻቸውን በአገልግሎቶቻቸው ማርካት እንድችሉ ሰራተኞችና ተቋማት በሥራ ላይ ሥነ- ምግባር የታነጹ ሆነውና በቴክኖሎጂ ታግዘው በፍጥነትና በጥራትና አገልግሎት እንድሰጡ በሥራ ላይ ሥነ-ምግባር መቃኘት እንደሚገባውቸም ተጠቅሷል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩም የሥራ ስነ- ምግባር እና የሃብት ማሳወቅና ምዝገባ አፈፃፀም መመሪያ ሰነዶች የቀረቡ ሲሆን በቀረቡ ሰነዶች ላይ በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ታደሰ አይበራ ማጠቃለያና የስራ መመሪያ ተሰጥቷል ።

በመጨረሻም የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ቅጽ ከዞኑ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ቡድን ጋር ርክብክብ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ የሃብት ምዝገባ ተደርጎ ይጠናቀቃልም ተብሏል፡፡

በዉቢት ደበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *