advd

Spread the love

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ6ኛው ዙር ስልጠና የሚወስድ 50 ሰልጣኝ ዲፕሎማቶች ስልጠና አስጀምሯል።

በስልጠና ማስጀመሪያው የሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ንጉስ ታደሰ እንዳሉት ፣ ዩንቨርስቲው በዲፕሎማሲ ዘርፍ በቂ ስልጠና መስጠት የሚያስችል አቅምና ልምድ አለው። ዩኒቨርስቲው ዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል ከፍቶ ተማሪዎችን እያሰለጠነ ይገኛል ብለዋል።

ሰልጣኝ ዲፕሎማቶችም ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታን መረዳት የሚያስችል እውቀት ይዘው እንደሚወጡ ገልፀዋል።

ሰልጣኝ ዲፕሎማቶች በፖሊሲ፣ በንድፈ ሀሳብና ተግባር ተኮር ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ተጠቁሟል።

በስልጠና ማስጀመሪያ ፕርግራም ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲኦን ጢሞቲዮስ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ እና የሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ንጉስ ታደሰ ተገኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአምስት ዙር ሰልጣኝ ዲፕሎማቶችን አሰልጥኗል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *