




”የጉባ ብስራቶች፣የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ የዉይይት መድረክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ አውራዳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በህዝባዊ የውይይት መድረክ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ እንደገለጹት ፤ሀገር የምትመራው በመደመር መንግስት አስተሳሰብ ነው።
ሀገሪቱን የሚመራው የመደመር መንግስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት ውስብስብ ችግር በማላቀቅ ህዝቦችን እያሳተፈ ቀን ከሌሊት በትጋት በመስራት ተጨባጭ ድሎችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ነው አቶ የሺዋስ አለሙ የገለጹት።
መንግስት በርካታ የልማት ፕሮጀክቶችን በማስጀመር እውን እያደረገ መሆኑን ጠቁመው ከዚህም የጉባ ብስራቶች የኢትዮጵያ የታሪክ እጥፋት እየቀየረ አንገቷን ቀና እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሀገሪቱን ካደጉት ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የመደመር እሳቤን ማስረጽ ይገባል ያሉት አቶ የሺዋስ አለሙ፤ የመደመር መንግስት ከህዝብ የተወለደ በመሆኑ ህዝብን በማዳመጥ የተጓደሉ ነገሮች ላይ ቤተሰባዊ ውይይት በማድረግ ጥያቄዎቻቸውን እየመለሰና እየፈታ ይገኛል ነው ያሉት።
ህዝብን ማዳመጥና ከህዝብ ጋር መመካር የመደመር መንግስት ልዩ ባህርይ ስለሆነ ይህ መድረክ ተዘጋጅቷል ስሉ ጠቅሰዋል።
በክልላችን ሠላሙን በማሰጠበቅ፣በተለያዩ ኢንቬቲቦች ተጨባጭ ዉጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።
የክልሉን ዕምቅ አቅም የለየ ዕቅድ በማቀድ ባለን ጸጋ ልክ ለመልማት የሚያስችል ክልላዊ መጠነ ሰፊ ዕንቅስቃሴ በሁለም ዘርፍ እየተደረገ ስለመሆኑ አቶ የሺዋስ ዓለሙ ገልጸዋል።
የካፋ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ታከለ ታምሩ በውይይቱ ባደረጉት ንግግር በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ ሀገር ለመፍጠር በየደረጃው የሚገኙ ህዝቦችን ማዳመጥ አስፈላጊ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ለትውልዱ የተሻለች እና ተምሳለት የሆነች ሀገር፣ክልልና ዞን ብሎም ከተማን ለማስረከብ ህዝብ፣መንግስትና ፓርቲ በተቀናጀ መልክ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዞኑ ብሎም በአውራዳ ከተማ የህዝቦችን የልማት አቅሞችን በመጠቀም በርካታ የተለያዩ የልማት ስራዎች እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተፈቱ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ታከለ የተጀመሩ ሥራዎችን ለማላቅ ለሌሎች የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የብልጽግና ፓርቲ እሳቤውን በመተግበር ይሰራልም ብለዋል።
በችግር ውስጥ የተወለደ ብልጽግና ፓርቲ የሚያጋጥሙ ውጫዊ እና ውስጣዊ ችግሮችን በመቋቋም እንደሀገር ሰፊ ድሎችን እያስመዘገበ እንደሚገኝም የአውራዳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታረቀኝ ኃይሌ ገልጸዋል።
ፓርቲዉ አዳዲስ ኢንሼቲቭ እየቀረጸ ለሀገር ብልጽግና ጉዞ መሠረት የሚጥሉና የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን ህዝቦችን እያሳተፈ እየሰራ ይገኛል ያሉት ከንቲባው፤ በከተማችን አውራዳ ሰፊ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው ብለዋል።
በህዝባዊ ውይይት መድረኩ የአውራዳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታረቀኝ ኃይሌ ለመወያያ የተዘጋጀ መነሻ ሰነድ እያቀረቡ የሚገኙ ሲሆን ከሚቀርበው ሰነድ መነሻ የጋራ ውይይት የሚደረግ ይሆናል።
