




በዳውሮ ዞን ያለውን አጠቃላይ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ማዕከል ያደረገ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለጹት፤ ውይይቱ የዞኑን አሁናዊ ሁኔታ በጥንካሬና በድክመት በመፈተሽ አመራሩን ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በከተማና በገጠር የሚነሱ የሕዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በብቃት ለመመለስና ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችሉ አቅጣጫዎች መከተል አለብን ብለዋል።
በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ በበኩላቸው፤ የአመራሩን አቅም በመገንባትና ህዝባዊ መሰረቱን በማጠናከር ረገድ መሰል መድረኮች ያላቸውን ፋይዳ አጽንኦት መስጠታቸዉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
በመድረኩ የክልል፣የዞንና የወረዳ /አስተዳደር ፊት አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
