በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ውጤታማ መሆናቸውን የታርጫ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ ።

Spread the love

በታርጫ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ያሉ የልማት ስራዎችን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ወጣቶቹ በተሰማሩባቸው የእንቁላል ጣይ ዶሮ በቀን ከ450 በላይ እንቁላል እያገኙ መሆናቸውን ለርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ዞኖች አንዷ በሆነችሁ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

የሌማት ትሩፋት አካል የሆነው የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ በተዘጋጁ 4 ሼዶች 20 ወጣቶች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው ውጤታማ መሆናቸውን የከተማው ከንቲባ አቶ ዳዊት ወንድሙ ተናግረዋል ።

በዚሁ የዶሮ ክላስተር በተሰማሩ ወጣቶች የተገኘው ውጤት የናረውን የእንቁላል ምርት ዋጋ በማርገብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛልም ብለዋል አቶ ዳዊት ።

አሁን ላይ በከተማው የእንቁላል ዋጋ ከ10_12 ብር እየተሸጠ መሆኑን በመግለጽ ለወጣቶቹም ያገኙትን የእንቁላል ምርት የገበያ ትስስር ለመፍጠር የመሸጫ ሼዶችን በመገንባት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ተናግረዋል ።

አሁን ላይ በዶሮ ክላስተር ካሉት 4ሼዶች በጨማሪ 3 ሼዶች ተገንብተው ለአገልግሎት ብቁ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

ወጣት ምንተስኖት በቀለ የሌማት ትሩፋት የዶሮ እርባታ ማህበር በመመስረት አምስት አባላትን በመያዝ 510 ዶሮዎችን እያረባ እንደሚገኝ ተናግሯል።

ወጣቱ አሁን ላይ በቀን ከ450 በላይ እንቁላል እንደሚያገኝና በ10 ብር ለህብረተሰቡ እያቀረበ እንደሚገኝም ተናግሯል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪም በከተማው እየተከናወነ ያለውን የከተማ ኮሪደር ልማት ስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም የአዲስ ፋና ሞዴል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤት ግንባታ አጀማመር ተመላክተዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *