ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ በማድረግ የሴቶችን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የታርጫ ማዕከል መሠረታዊ ድርጅት ኮንፍራንስ አካሂዷል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ሊግ ኃላፊ ወ/ሮ ሰብሌ ፀጋ አየለ እንደገለጹት የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ በገነባቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተግባራት ላይ በተደራጀ መንገድ ሴቶች ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል እየተሰራ ይገኛል።

በተለይም ሴቶች በሁሉም ዘርፎች በሚያካሂዱት ተግባር ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ለስትራቴጂክ ዕቅድ ኃይል መሆናቸውን በመገናዘብ ግንባር ቀደም እንዲሆኑም ይፈለጋል።

ሰው ተኮር የሆነ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲቻል እንደምግብን ከጓሮዬና የሌማት ትሩፋት የመሳሰሉ ተግባራትን በመቅረጽ እየተንቀሳቀሰ እንዳለም ወ/ሮ ሰብሌ አብራርተዋል።

አሁን ላይ የመሠረታዊ ድርጅት አድማስ በማስፋት አባሎችን በማብቃትና በማጠናከር እንዲሁም አባል ያልሆነ ሴቶችን ግንዛቤ በማሳደግ ሊሠራ እንደሚገባም ተገልጿል።

ቀጣይ ለሚካሄደው ግብ ማሳኪያ ይሆን ዘንድ የፋይናንስ አቅም በማጠናከር ከጥገኝነት ለመላቀቅ በትኩረት ሊሠራ ይገባልም ተብሏል።

በኮንፈራንሱ የተገኙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፀሀይ ዳርጫ በበኩላቸው በውጤት የታጀበ ሥራ ለማየት እንዲቻል ጠንካራ ሕዋስ መገንባትና ቅንጅታዊ አሰራር መዘርጋት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሊጉ አባል ሴቶች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ግንባር ቀደም መሆን መቻል ተገቢ መሆኑን የተናገሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵዮያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ቤተልሔም ዳንኤል ናቸው።

በኮንፈራንሱ የ2017 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ቀርቦ በጋራ ተገምግሟል።

በተሻሻለው የሴቶች ሊግ አሠራርና አደረጃጃት መመሪያ ላይ ተወያይተውበታል።

መመሪያው የፓርቲው አባላት መዋጮን በተመለከተ ማሻሻያ መደረጉን የሚያሳይ ሲሆን ዓላማው የፓርቲውን የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር ነው።

ሊጉን አጠናክረው ለማስቀጠል፣ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብና ተቀናጅቶ በመሥራት ግንባር ቀደም ለመሆን ተሳታፊዎች በመግባባት መድረኩ ተጠናቅቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *