በአንደኛው መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች የህዝቡን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ ቢሆንም በጅምር ያሉት በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ በተቀመጠው አቅጣጫ ተፈጻሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው።

Spread the love

” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ከማሻ ከተማ ከህዝቡ ከተውጣጡ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ መድረኩ የተመቻቸው ሰው ተኮር የሆነው የብልጽግና ፓርቲ በመጀመሪያው መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መፈተሽና

በሁለተኛ ዙር ጉባኤ የተመላከቱ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ከህዝቡ ጋር መምከር በማስፈለጉ ነው ብለዋል።

ፓርቲው ህዝቡን በማወያየት ሀሳብና አስተያየት በመቀበል ተቀራርቦ የሚሰራ በመሆኑ ከህዝቡ የሚነሱ የመልማት ጥያቄዎችን ትኩረት ሰጥቶ ይሰራልም ሲሉ አክለዋል።

የሸካ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ዓለሙ በበኩላቸው ባለፉት አመታት በሀገር ደረጃ የተስተዋለውን ያለመስማማት ተከትሎ በውስጥም ሆነ በውጪ የሚደረጉ ሹክቻዎችና ጫና የነበራትን ሀገር መኗን የሚፈለገውን ውጤት አኮላሽቷል ብለዋል።

ይሁን እንጂ እነዚህን ጫናዎችን በመቋቋም ድል እያስመዘገበ የመጣውን የብልጽግና ፓርቲ በቀጣይ ለሚሰሩ ተግባራት ህዝብን በማወያየትና በመቀራረብ ለህዝቡ ይሰራል ብለዋል።

የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰራዊት አየነው በለውጡ መንግስት እስከአሁኑ ድረስ የተሰራውን ስራና የቀጣይ ተግባራት ሪፖርት አቀርበዋል።

በ2016 በጀት ዓመት የተመዘገቡ የከተማ መሠረተ ልማቶችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባው የማሻ ሆስፒል ቀዶ ጥገና መጀመሩ ሌላ ብስራት መሆኑንም አመላክተዋል።

ያደሩና አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ የሆኑ የመንግስትና የግል ኢንቨስትመንት ተቋማትን ሂደት ገምግመን ለውጤት እንሰራለንም ብለዋል ሲል ማሻ ኤፍኤም ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *