ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ አመታት ውስጥ የተዘነጉ አካባቢዎች ፍትሐዊ ተሳትፎና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ተግባራትን አከናዉኗልናል። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ ድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በሰልፉ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት የለዉጥ ዓመታት የብልፅግና ፓርቲ በቀደሙት ስርአት የተረሱ አካባቢዎችን በማስታወስ እኩል የልማትና መልካም አስተዳደር ተሳታፊ እና ተጠቃሚ በማድረግ ከፍተኛ ለውጥ ካስመዘገበባቸው አካባቢዎች የምዕራብ ኦሞ ዞን አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአካባቢዉ በመገኘት እና የህብረተሰቡን ችግር በመረዳት በዞኑ ሱሪ ወረዳ ያስገነቡት ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ እና ሌሎች ተቋማት ለህብረተሰቡ ጥያቄ ከመመለስ ባለፈ ለአካባቢው ትኩረት መሰጠቱን አስገንዝበዋል።

በዞኑ አልፎ አልፎ የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ሚሊሻ በማሰልጠንና የፀጥታ መዋቅሮችን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

‎በብልጽግና መካከል ለዘመናት የህዝብ ጥያቄ የነበረውን በክልል የመደራጀት መብት ከማረጋገጥ በተጨማሪ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ አንዱ የፓርቲ ውጤት ነው ሲሉ ገልፀዋል ሁሉም ብልጽግናን እንዲመርጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ አመታት ውስጥ የተዘነጉ አካባቢዎች ፍትሐዊ ተሳትፎና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ተግባራትን አከናዉኗልናል ስሉ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ባደረጉት ንግግር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ባለፉት ዓመታት ህዝቡ በሰጠን ይሁንታ መሰረት ላከናወንነው ተግባራት ከጎናችን መሆኑን በይፋ ስለገለጻችሁ አመሰግናለሁ ብለዋል።

ምንም እንኳ ፓርቲያችን ከውስጥና ከውጭ ተላላኪዎች በርካታ ፈተናዎች የተደቀኑበት የነበር ቢሆንም በጽኑ መሠረት ላይ የተመሠረተ ፓርቲ በመሆኑ ፈተናዎችን ወደ ድል በመቀልበስ እየተሻገረ ይገኛልም ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህም ፓርቲያችን ተቀብሮ የቆየውን የባህር በር ጉዳይ ወደ አደባባይ ከማምጣቱም ባሻገር የጉባ ብስራቶች በሚል ይፋ ያደረጋቸው የ30 ቢሊየን ብር ፕሮጀክቶች ትልቅ ማሳያ ናቸውም ብለዋል።

‎ሀገር ብልፅግና ፓርቲ ከለውጡ በፊት የነበሩ እንቅፋቶችን እና ፈተናዎችን በድል በመሻገር የሀገራችንን ህልውና በማስጠበቅ በአለማችን እና በአፍሪካ ደረጃ እውቅናን የተቸረው ብልጽግና ፓርቲ ብቻ ነው ብለዋል ።

‎የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ታምሩ ቦኒ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው ዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ትሩፋት መሆኑንና በመዋቅር የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት እንደሆነም ተናግረዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አመታት የዞኑን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ በኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች እንዲሁም በዲፕሎማሲ ውጤታማ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን በመግለፅ መላ የብልፅግና አመራርና አባላት ብልፅግና ፓርቲ ያሳያቸውን ትሩፋቶች በማየት ቀጣይ የፓርቲውን ራዕና ዕቅዶች ለማሳካት በ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ ድል እንድጎናጸፍ መስራት ይጠበቃል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *