ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በአዕምሮ የበለፀገ ማህበረሰብ መገንባት ሲቻል መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

የክልሉን የምግብ ስርዓት ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት የሚያስችል ሀሳብ ላይ ከባለድርሻ ተቋማት ከተወጣጡ አካላት ጋር አዉደ ጥናት ተደርጓል።

በክልሉ የሚዘጋጀዉ ፍኖተ ካርታ ለቀጣይ አምስት አመት የሚያገለግል እንደሆነ ተጠቅሷል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጰያ ህዝቦች ክልል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተዘጋጀ ያለውን የምግብ ስርዓት ና ኒዉትርሽን ፍኖተ ካርታ ማዘጋጃ ስልጠና ላይ የተገኙት የክልሉ ግብርና ቢሮ ም/ሃላፊ ና የእርሻ ሀርፍ ሃላፊ አቶ አሸናፍ ክንፈ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚረጋገጠዉ በቁሳዊ ሳይሆን በአዕምሮ የበለፀገ ማህበረሰብ መገንባት ስንችል ነዉ ስሉ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የምግብ ስርዓት ሽግግርና ኒዉትርሽን የክላስተር አንድ አስተባባሪ አቶ መሠረት ፀጋዬ እንደገለፁት የሚዘጋጀዉ ፍኖተ ካርታ ትኩረቱ የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ እንደሚገልጥ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግርና ኒዉትርሽን ሰባት ዋና ዋና ክላስተሮች እንዳሉት ያብራሩት አቶ መሠረት ፀጋዬ በክልሉ የሚዘጋጀዉ የምግብ ስርዓት ፍኖተ ካርታ ክልሉን የሚመጥን የተፈጥሮ ጸጋን ያገናዘበና ሊተገበር የሚችል መሆን አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ምግብ ሽግግር ከተባበሩት መንግስታት በተሰጠዉ አቅጣጫ መሠረት የኢትዮጵያ የምግብ ስርዓትን በዚሁ ሁኔታ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የምግብ ስርዓት ሽግግርና ኒዉትርሽን የክላስተር ስድስት አስተባባሪ አቶ ሰዉነት ገ/ፃድቅ ፍኖተ ካርታዉ ከምርት ማምረት ጀምሮ የአመጋገብ ስርዓትና የፖሊሲ ጉዳዮች እንድሁም የአየር ንብረት ለዉጥ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን ያካተተ ነው ብለዋል።

የክልሉ ምግብና ስርዓተ ምግብ ማስተባበሪያ ዩኒት አስተባባሪ አቶ ማትዮስ ማልዳዬ እንደገለፁት የሚዘጋጀዉ የምግብ ስርዓት ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ለአምስት አመት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አስረድተዋል።አክለዉም እቅዱ ተግባራዊ በሚሆንበት ሰዓት ተቋማት በቅንጅት በመስራት በምግብ ስርዓትና ኒዉትርሽን ላይ መሠረታዊ ለዉጥ በማምጣት በክልላችን የበለጸገ ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ይገባል ብለዋል።

ክልላዊ የምግብ ስርዓት ፍኖተ ካርታ መዘጋደቱ በምግብ ስርዓትና ኒዉትርሽን ዙርያ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተሻለ ሁኔታ ለመቅረፍ ያግዛል ያሉት ደግሞ በክልሉ የምግብ ስርዓትና ኒዉትርሽን የብዝሃ ሰክተር አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ አስረሳሽ ሰበታ ናቸዉ።

በክልሉ የምግብ ስርዓት አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ አቤኮዬ ሽፈራሁ የምግብ ስርዓት ፍኖተ ካርታን ማዘጋጀት የምግብ ስርዓት ዓላማን እውን ለማድረግ የሚያግዝ ስለመሆኑ ተናግረዋል ።

ብዝሃ ሴክተሮች በቅንጅት የምግብ ስርዓትና ኒዉትርሽን ፕሮግራሞችን እውን ማድረጋቸው የሰዎችን ሰብዓዊ መብት ለመጠበቅ አጋዥ እንደሆነም ተናግረዋል ።

በጌጠነሽ ገበየሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *