



መጸሐፉ የካፈቾ ህዝብ ባህል እና ታሪክ ላይ ያተኮረ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
የመጸሐፉ ደራሲ አቶ አሰፋ ገብረማርያም መጽሐፉ ሰባት ምዕራፎችና 3 መቶ 36 ገጾች ያሉት እንዲሁም የካፈቾ ባህል እና ታሪክ ላይ ያተኮረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የካፈቾ ብሔር ማንነትን፣ የጎንጋ ህዝቦች ትስስርን፣ ጥንታዊ የካፋ መንግስት አመሰራርንና ሌሎችንም ሀሳቦች ስለማካተቱ ገልጸዋል፡፡
መጽሐፉ ለታዳጊ ደራሲዎች መነሻ እንደሚሆን ገልጸው ፤ ለህትመት እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ የካፈቾ ባህልና ታሪክ በአካባቢው ተወላጆችና ምሁራን መጻፉ ለጀማሪ ጸሐፍት ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም የህዝቡን ባህልና ታሪክ ለአዲሱ ትውልድ ለማሰተላለፍ በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የዞኑ አስተዳደር ድጋፉን እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል፡፡
በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ ከተገኙ ታዳሚዎች መካከል አቶ ብርሃኑ ሀይሌና አቶ ፍቅሬ ገብሬ መጽሐፉ ታሪክን ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍና ለማጉላት ፈይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ የካፋ ዞን አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል ሲል ቦንጋ ኤፍኤም 97.4 ዘግቧል፡፡
