በግብርናው ዘርፍ የ7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

Spread the love

6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በውጭ ግንኙነት፣ በሠላምና ፀጥታ እንዲሁም የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎች ከምክር ቤት አባላት ተነስተዋል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በሰጡት ምላሽና ማብራሪያቸው በግብርናው ዘርፍ በ2017 ዓ.ም 7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት መመዝገቡንና ከዓመታዊ ጥቅል እድገት 2 ነጥብ 3 ድርሻ እንዳለው አመልክተዋል። የግብርናው ዘርፍ ከለውጡ ማግስት በኋላ ከፍተኛ ለውጥ እና እድገት ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

በ2010 ዓ.ም የስንዴ ምርት 47 ሚሊዮን ኩንታል ይመረት እንደነበር አንስተው፤ በ2017 ዓ.ም ከ280 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ ማምረት መቻሉ ትልቅ ለውጥ እንደሆነ ተናግረዋል። የስንዴ ምርቱ እድገት የበርካታ አድካሚ እና አታካች ስራዎች ውጤት ነው ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *