
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከዚምባብዌ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ምቱሊ ኢንኩቢ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም፤ ሁለቱ ወገኖች በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ወሳኝ የኢኮኖሚ ፖሊሲና የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ምቱሊ ኢንኩቢ በዚሁ ወቅት፤ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ስኬታማ የኢኮኖሚ ስትራቴጂዎች ልምድ መውሰድ እንደምትፈልግ ገልጸዋል፡፡
አቶ አህመድ ሺዴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከዚምባቡዌ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ስኬታማ የኢኮኖሚ ስትራቴጂ ትግበራ ልምዷን ለማጋራት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ የሀገራቱን የኢኮኖሚ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከርና የልምድ ልውውጦችን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በቀጣይ የልምድ ልውውጥና ትብብርን ለማመቻቸት የሚያስችል የቴክኒክ የስራ ቡድኖችን ለማቋቋም ከስምምነት መድረሳቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።
