


ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ ውስጥ ተገንብተው የተጠናቀቁ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መርቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
በቀጣይ ለሚከናወኑ አዳዲስ የልማት ስራዎች መነሻ የሚሆን የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓትም እንደሚካሄድም ተመላክቷል።
ይህ ጉብኝት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ፣ በዞኑ ዋና ከተማ ታርጫ ሲደርሱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸዉ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
