የህዳሴውን ግድብ በመጠናቀቁ በክልሉ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ይካሄዳል:-አቶ የሺዋስ ዓለሙ

Spread the love

የህዳሴውን ግድብ በመጠናቀቁ በክልሉ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ይካሄዳል:-አቶ የሺዋስ ዓለሙ

የዘመናት ህልም፣ የሉዓላዊነት አርማና የ”ይቻላል” መንፈሳችን ማሳያ የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ህዝቦች በታላቅ ደስታ ላይ ይገኛል። የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ይህን ታሪካዊ ድል በመላው ክልሉ በሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች በደማቅ ህዝባዊ ሰልፎች ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቋል ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ፣ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን፣ ሰልፎቹ “በህብረት ችለናል!” በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።

አቶ የሺዋስ እንዳሉት፣ “ይህ ግድብ የሉዓላዊነታችን አርማ፣ ‘በህብረት ችለናል’ የሚለው መሪ ቃላችን ህያው ምስክር ነው። ድሉ የሁላችንም ነው። ይህንን ድል ስናከብር ጠላቶቻችን የሚርዱበት፣ ወዳጆቻችን ደግሞ የሚኮሩበት ታላቅ የአንድነትና የጥንካሬ መገለጫ እንዲሆን እናደርገዋለን። ይህ ድል ለቀጣይ የብልጽግና ጉዟችን የማይነጥፍ የሞራል ስንቅ የሚሆነን ታላቅ ታሪካዊ ክስተት ነው” ብለዋል።

ታላላቆቹ የድጋፍና የደስታ ሰልፎች በሚከተለው የጊዜ ሰሌዳ ይካሄዳሉ ስሉም ገልጸዋል፦

ከመስከረም 04 ጀምሮ በክልሉ ባሉ ቀበሌዎች የድጋፍ ስልፉ የተካሄደ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የወረዳና የከተማ አስተዳደር ማዕከላት እየተካሄደ እንደሆነ ኃላፊዉ ጠቅሰዋል።

በመስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም: በሁሉም የዞን ማዕከላት የሚካሄድ ሲሆን መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም: በክልል ደረጃ በቦንጋ ከተማ በሚካሄድ ታላቅና ደማቅ ስነ-ስርዓት ይከበራልም ብለዋል።

መስከረም 9 በክልል ደረጃ በሚካሄደዉ የተለያዩ መረሃ ግብሮች እንዳሉት የገለጹት ኃላፊዉ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ከክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የተዉጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች እና የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።

በመሆኑም ቢሮው ለመላው የክልሉ ህዝብ የክብር ጥሪ አቅርቧል። ህዝቡ ከህፃናት እስከ አዛውንት፣ በየቀበሌውና በየከተማው በነቂስ በመውጣት የዚህ ታሪካዊ ድል ባለቤት መሆኑን እንዲያረጋግጥ፣ ደስታውን በጋራ እንዲገልጽና ለዓለምም የማይናወጥ አንድነቱን እንዲያሳይ ጥሪ ቀርቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *