የወጣቶች ተሳትፎ በሚዛን አማን ከተማ

Spread the love

የምርጫ ካርድ መውሰድ ሀገራዊ ኃላፊነት እና ግዴታን መወጣት ነው ሲሉ በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የሚኖሩ ወጣቶች ገለጹ

ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫን ለማካሄድ ዜጎች በየአካባቢያቸው በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው በመመዝገብ የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ይገኛል።

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ቤንች ሸኮ ቴቪ ያናገራቸዉ ወጣቶች መካከል ወጣት ቡዛብ ደመላሽ ፣ ወጣት ሲምኦን ፣ ወጣት ሙሴ ኤርማያስ እና ሌሎችም እንደገለፁት የምርጫ ካርድ መውሰድ ሀገራዊ ሀላፊነት እና ግዴታን መወጣት ነው ብለዋል።

እነሱም ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሀገርን ወደ ዕድገት ጎዳና ሊያሻግር የሚችል ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ በየአካባቢያቸው በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት መውስዳቸውን ገልፀዋል።

በመሆኑም መላው ወጣቶች በነቂስ ወጥተው በአካባቢያቸው ወደ ሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ሄደው በመመዝገብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ አንድም ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ በሌላ በኩል ደግሞ የምርጫ ካርድ በመውሰድ የዜግነት ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ተመዝግበው የምርጫ ካርድ የውሰዱትም ካርዳቸውን በአግባቡ በማስቀመጥ የምርጫ ጊዜው ሲደርስ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ሀገርን ሊመራ ይችላል የሚሉትን ፓርቲ ሊመርጡ እንደሚገባም ተናግረዋል ሲል ቤንች ሸኮ ቴቪ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *