በዞኑ 364 የግል ባለሀብቶች በተለያዩ የእንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራታቸው ተገለጸ።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን 364 የግል ባለሀብቶች በተለያዩ የእንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራታቸውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ገልጸዋል።

ኢንቨስትመንት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት እና የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የዞኑ ዋና አሰተዳዳሪ ጨምሮ መግለፃቸውን የካፋ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

የካፋ ዞን ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ የኢንቨስትመንት ምክክር ፎረም ቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

የፎረሙ ዓላማ በዋናነት በግሉ ኢንቨስትመንት ዙሪያ የሚስተዋሉትን ማነቆዎች ለይቶ ለመፍታት ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑ ተመላክቷል።

የካፋ ዞን ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን መሸሻ ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ባሉበት ወቅት ለአንድ ሀገር ዕድገትና ለውጥ የኢንቨስትመንት ድርሻው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

በዞኑ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሀኔታ በመፍጠር በሁሉም ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት እንዲከናወኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ አመላክተዋል።

ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር እና ውጤታማ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ አርሶ አደሩ ዘንድ ተደራሽ ለማድረግ ኢንቨስትመንቶች የበኩላቸውን ደርሻ ሊወጡ እንደሚገባም የመምሪያ ኃላፊው አክሏል።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በመክፈቻ ንግግራቸው እንቨስትመንት ለአንድ ሀገር ዕድገት የጎላ ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።

364 የግል ባለሀብቶች በዞኑ በተለያዩ የእንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራታቸውን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪ ውጤታማ በሚሆኑበት ጉዳዮች ላይ የዞኑ መንግስት ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል::

የተሻለ ሥራ በመስራት ማህበረቡን የሚጠቅሙ እንቨስትመንቶች የመኖራቸውን ያክል በውላቸው መሰረት የተሰጣቸውን መሬት በአግባቡ የማያለሙና የሥራ ዕድል በበቂ የማይፈጥሩ፣ ምርትና ምርታማነት የማያረጋግጡ ባለሃብቶች መኖራቸውንም ዋና አስተዳዳሪ አንስተው ይህም በቀጣይ መስተካከል እንዳለበት ጠቁሟል::

ለምክክር ፎረም ውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ የመምሪያ ም/ኃላፊና የእንቨስትመንት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ገ/ስላሴ እያቀረቡ መሆናቸዉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *