የአመራር አስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ማጠናከር የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት እንደሚገባ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ

Spread the love

በሸካ ዞን የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ያለመ የአመራር የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሂዷል

የአመራር አስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ማጠናከር የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እንደሚያስችል በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ፍቅሬ አማን ገልጸዋል ።

የፓርቲው የለውጥ ጉዞ የታለመለትን ግብ እንዲመታ፣ አመራሩ የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎችን በላቀ ዝግጁነትና በጽኑ ቁርጠኝነት ሊያከናውን እንደሚገባም አሳስበዋል።

በተለይም የሚታዩ የአፈጻጸም ክፍተቶችን ለመድፈን አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል ።

በዞኑ እስካሁን የተመዘገቡ የሰላምና የልማት ስኬቶችን በዘላቂነት ለማስቀጠል የአመራሩ የቅርብ ክትትልና የሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም አቶ ፍቅሬ አጽንኦት ሰጥተውበታል።

አክለውም በሸካ ዞን የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችንና ሰፊ የልማት አቅሞችን በውጤታማነት በመጠቀም፣ የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፓርቲያችን ብልፅግና በአብላጫ ድምፅ እንዲያሸንፍ አመራሩና አባላቱ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል አቶ ፍቅሬ ።

በምርጫው ድምጽ ለመስጠት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ድምጽ እንዲሰጡ የማድረግ ስራም እንዲሰራ አንስተዋል ።

በተለይም የተዛቡ ትርክቶችን በመመከትና የፓርቲውን ድሎች ለሕዝብ በማስተዋወቅ ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች በትኩረት ሊመሩ እንደሚገባም አመላክተዋል ።

የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታና ወቅታዊ አዝማሚያዎችን በጥልቀት በመተንተን፣ ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ተገቢውን ምላሽ በአፋጣኝ መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ተሳታፊ አመራሮች በበኩላቸው የታዩ የአፈጻጸም ክፍተቶችን ለማረም እና ከሕዝብ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ፈጣንና ተገቢ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሰሩ ገልጸዋል ሲል የሸካ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *