ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ ጥሩ አፈፃፀም ካላቸው ሀገራት መካከል ነች

Spread the love

25ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የፋይናንስ ሚኒስትሮች ስብሰባ በኬኒያ ናይሮቢ በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተሳተፉ ሚኒስትሮች ዲጂታል ትስስርን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2023 ስለፀደቀው የዲጂታል ውህደት እና የፖሊሲ ማዕቀፍ ሚኒስትሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም ሀገራት ጥሩ አፈጻጸም በማስመዝገብ ላይ መሆናቸው የተመላከተ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ጥሩ አፈፃፀም ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ነች ተብሏል፡፡

በምክክሩ የተሳተፉት የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በዲጂታል ውህደት እያስመዘገበች ያለችውን ዕድገት ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ የቴሌኮም ዘርፎችን ነፃ ማድረግ፣ የግል መረጃ ጥበቃ እና የሳይበር ደህንነት ህጎችን በማውጣት በርካታ ተግባራት ማከናወኗን ጠቁመዋል።

ከ19 ሚሊየን በላይ ዜጎች በዲጂታል መታወቂያ ስርዓት በመመዝገብ ውጤት ማምጣት መቻሉን ማብራራታቸውን ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *