




የፍቃድ ስምምነቱን የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ እና የኩባንያዎቹ ስራ አስፈጻሚዎች ተፈራርመዋል፡፡
ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 27ኛ መደበኛ ስብሰባ የብሮሚን፣ የግራናይት፣ የድንጋይ ከሰል እና የደለል ወርቅ ማዕድናትን ለማልማት በተወሰነው ስምምነት መሰረት ነው፡፡
ለኩባንያዎቹ ፈቃድ የተሰጠው የማዕድን ምርመራ ፈቃድ ወስደው የምርመራ ስራ በመስራት እና ከእዚህ በፊት የተሰሩ ጥናቶችን መረጃ በመጠቀም ወደ ምርት መግባት የሚያስችል የቴክኒክና የፋይናንስ መረጃዎችን አሟልተው በመገኘታቸው መሆኑም ተገልጿል፡፡
የማምረት ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎችም ጄሬህ ኬሚካል ኢንዱስትሪያል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ራፊቅ ሁስኒ ፋሪስአልቀብ፣ ሰኮያ ማይኒንግ እና ፕሮሰሲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና ኦሮሚያ ማይኒንግ አክሲዮን ማህበር ናቸው።
ኩባንያዎቹ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩም ተገልጿል።
መንግስት ለማዕድን ዘርፉ በሰጠው ትኩረት መሰረት የባለሀብቶችን የማልማት ጥያቄ ተቀብሎ ተገቢውን ምላሽ እየሰጠ መሆኑም ተጠቁሟል።
በመሆኑም ኩባንያዎቹ ወደ ስራ እንዲገቡና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ማዕድን ሚኒስቴር ማሳሰቡን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
