




ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው በአለም አቀፉ የልማት ማኅበር(አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ናይሮቢ ኬንያ ገብተዋል።
ጉባኤው ማኅበሩ ደጋፊዎች እና ተባባሪ አካላት በአፍሪካ የልማት የገንዘብ ድጋፍ ቀዳሚ የትኩረት መስኮችን ለማመላከት እና አፅንዖት ለመስጠት ያለመ ሲሆን የገንዘብ ድጋፍ አቅራቢዎች በ21ኛው የማኅበሩ ዘመን ድጋፋቸውን ለመጨመር በፅኑ እንዲያጤኑ የማሳሰብ አላማ ያነገበም ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ይህ ድጋፍ የአፍሪካን የልማት ተግዳሮቶች እና መልካም እድሎች በተገቢው መንገድ ለማስተናገድ እጅግ አስፈላጊ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
