የክልሉ መንግሥት ያደረገው የአመራር ለውጥ የህዝብን ጥያቄ የሚመልስና ተገቢ ነው ሲሉ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ሰሞኑን ያከናወነው የአመራር ሽግሽግ፣ አዳዲስ አመራሮችን መመደብና ነባሮችን ማንሳት፤ የህዝብን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተወሰደ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

አስተያየት ሰጪዎቹ እንዳሉት፣ ጠንካራ መንግሥትና ፓርቲ ለመገንባት በየጊዜው የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚያዳምጥና ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የአመራር ስርዓት መዘርጋት ወሳኝ ነው ብለዋል።

በተለይም የአመራር ሹመትና ምደባው በእውነተኛ የማስፈጸም ብቃትና በትምህርት ዝግጅት ላይ የተመሰረተ መሆኑን የጠቆሙት ነዋሪዎቹ፣ የክልሉ መንግሥቱ ሴቶችንና ወጣቶችን ወደ አመራርነትና ውሳኔ ሰጪነት ለማምጣት የጀመረውን ጥረትም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በክልል ደረጀ የተጀመረው የአመራር ስምሪት በየደረጃዉ ባለዉ መዋቅር ተግባራዊ መሆን እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በአጠቃላይ ሹመቱና ሽግሽጉ ተገቢ መሆኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ አዲስ የተመደቡት አመራሮችም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃትና በህዝብ አገልጋይነት ስሜት እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በተከተል ወ/ሚካኤልና በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *