






ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 6ቱ ዞኖች የተወጣጡ የትምህርት ዘርፍ አመራሮችንና ባለሙያዎችን ያሳተፈ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም የሚገመግም መድረክ በተርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
አሁን ላይ የሚታየውን የትምህርት ስብራቶችንና ኪሳራን በመጋፈጥ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር ተገቢ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ ገልጸዋል።
አቶ አልማው እንደተናገሩት አሁን ላይ የሚታዩ መልካም ጅምሮችን አጠናክሮ በመቀጠል የነገ ሀገር ተረካቢ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት የሚያደርግ የትምህርት አመራር ስርዓት መዘርጋት የተቀናጀ ጥረት ሊኖር እንደሚገባም አሳስበዋል።
በምክክር መድረኩ በ2016 የትምህርት ዘመን እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት ተገምግመው ለቀጣይ የትምህርት ዘመን የትኩረት አቅጣጫ ላይ ዉይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።
ከትምህርት ንቅናቄ ጀምሮ እስካሁን የነበሩ ተግባራት ተሰፋ ሰጪ ዉጤቶች የታየባቸው መሆኑን አንስተው ለቀጣይ ጊዜያት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም ገልፀዋል።
የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የትውልድ መሠረት በመሆኑ ያጋጠመን የትምህርት ተሳትፎ ማነስ ላይ በቁጭት ሊሠራ ይገባል ብለዋል ኃላፊዉ።
ከውይይቱ መድረኩ ተሳታፊዎች ጋር በሚደረገው ምክክር የተሻለ አስተያየትና ግብአት እንደሚገኝ ይጠበቃል።
