በጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ላይ የተጀመሩ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በጎልማሶችና መደበኛ ባልሆነ ትምህርት አሰራርና አደረጃጀት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው በተፋጠነ ትምህርት ጋይድ ላይን፣ የጎልማሶች ክህሎት ማበልጸጊያና የመሠረታዊ ትምህርት ማመቻቸት ሥነ ዘዴ ትምህርት ላይ ያተኮረ ነው።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማር ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ደሰታ ገነሜ በወቅቱ እንደገለጹት፤በክልሉ የትምህርት ስራዓት ላይ ያለው ጉድለት በቤተሰብ፣ጎልማሳና በወላጅ በጋራ ጥምረት ለውጥ ለማምጣት በጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ላይ በተቀናጀ ሁኔታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

መጻፍ፣ማንበብና ማስላት የሚችል ጎልማሳ ልጁን ወደ ትምህርት ገበታ በመላኪ ሂደቱን በመከታተል በትምህርት ውጤታማነት ያለው አበርክቶ የላቀ በመሆኑ በክልሉ የተዘጉ የጎልማሶች ትምህርት ቤቶች በመከፈታቸውና ለዘርፉ ባለድርሻዎች የተለያዩ ስልጠናዎች በመሰጠታቸው በዘርፉ ለውጦች እየታዩ መምጣታቸውን አስረድተዋል።

ዶክተር ደስታ ገነመ በንግግራቸው ቀድም ሲል በተቀናጀ ሲመራ የነበረው የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት እና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት አደረጃጀት በአዲሱ ረፎርም በመምጣቱ የጋራ ግንዛቤ በመውሰድ የአማራጭ መንገዶችን በመቀየስ እስስከታች ስልጠናዎችን በማውረድ በዘርፉ ከአመለካከትና ከመረጃ ስርዓት ጋር የሚታየው ጉድሌት በማረም ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በዚህም ስራዎችን በየጊዜው በመከታተል እና በመገምገም ሞደል ከሆኑ ትምህርት ቤቶች ልምድ በመቀመር በጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ላይ የተጀመሩ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

እንደክልል የተፈጠነ ትምህርትና በጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ያነሱት የቢሮ ጎልማሳና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ ዳይሬክቶሬት አቶ አስረስ አዳሮ የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ተምሮ ያጠናቀቁ ተማሪዎች እና በሃይማኖት ተቋማት ተምረው ማንበብ መጻፍና ማስላት የቻሉት ብረሃነ ምዘና ተፈትነው 50 እና ከዚያ በላይ ያሙጡት ለቀጣይ ትምህርት ደረጃ ይዘጋጃሉ ብለዋል።

በክልሉ የዩንሴፍ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ካሳሁን ዱባሌ እንደገለፁት ፕሮግራሙ በመደበኛው የትምህርት ፕሮግራም የመማር ዕድል ያላገኙ እንዲያገኙ ለማስቻል በክልሉ በ14 ወራዳዎች ላለፉት ዓመታት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናወን መቆየቱን ተናግረዋል።

ፕሮግራም የቅድመ መደበኛ ትምህርትን የመደገፍ፣ ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ሕጻናትን ማምጣትና ግብአቶችን ማመቻች ጨምሮ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ላይ ዓላማ አድርጎ ይሰራል ብለዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ስልጠና የክልል፣ የዞንና የወረዳ ትምህርት አመራርና ባለሙያዎችን ጨምሮ የተፋጠነ ትምህርት መምህራን፤የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት አመቻቾችና ቡድን መረዎች እየተሳተፉ ናቸው።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *