
በዚህ ዓመት ብቻ 23 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት መውጣታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፤ በዚህ ዓመት ብቻ 23 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህ የማንሰራራት ትልቁ ማሳይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህ ስራ ሁላችንም ኩራት ሊሰማን ይገባል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ መለመን የለባትም ልጆቿ ተግተው ሰርተው ከልመና ራሳቸውን ማውጣት አለባቸው የሚለው እምነት ፍሬ እያፈራ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ዓመታት 27 ሚሊዮን ሰዎች በሴፍቲኔት የታቀፉ ተረጂዎች ነበሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እንዚህን ተረጂዎች ከሴፍቲኔት ነፃ ማውጣት አለበን በሚል በግብርና ንዑስ ዘርፍ ውስጥ እንደዋና ጉዳይ ተይዞ ሲሰራ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
በተሰራው ስራም ዘንድሮ 23 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት ወጥተዋል ብለዋል፡፡
ቀሪው ከ4 ሚሊዮን ያላነሰ ተረጂም ነጻ በማውጣት ኢትዮጵየን ሙሉ ለሙሉ የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች ሀገር ማድረግ አለብን ሲሉም ጠቅሰዋል።
