የካፋ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔዉን በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነዉ

Spread the love

ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው ይሄው መደበኛ ጉባኤ ያለፈውን 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 23ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃሌጉባኤ መርምሮ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ስብሰባውን ጀምሯል::

የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ በሚኖረው የ2 ቀናት ቆይታ የተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ የሚወያይ ሲሆን ከነዚህም መካከል የካፋ ዞን የአስፈፃሚዎች የ2017 ዓ/ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ማድመጥ: የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2017 ዓ/ም የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ማድመጥ እንድሁም አዳዲስ የቀበሌ መዋቅሮችን ውሣኔ ማስተላለፍና ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ቀርቦ በመወያየት ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል::

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ እንዳሻው ከበዴ የአስፈፃሚዎች የ2017 ዓ/ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እያቀረቡ ናቸው::

ጉባኤው ለ2 ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል መሆኑን

የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *